End Diabetes Stigma and Discrimination

Amharic – አማርኛ

:  እኔ/እኛ ከስኳር ህመም ጋ ተያይዞ የሚደርሰውን አድልዎ እና መገለል ለማስወገድ የ ሚከተሉትን በንቃት በመፈጸም አስተዋፅዖ ለማድረግ ቃል እንገባለሁ/እንገባለን፡-

ማንኛውም አይነት የስኳር ህመም ያላቸውን ሰዎች በማክበር

በስኳር ህመም ምክንያት የሚደርስ መገለል መኖሩን መገንዘብ እና የሚያስከትለውም ጒዳት እንዳለ

የስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች ያለኝ/ያለን ጭፍን ጥላቻ እውቅና በመስጠት በመታገል ።

ስለ ስኳር ህመም ወይም ስኳር ህሙማን የምናደርገው ተግባቦት ከፍረጃ የጸዳ፣ትክክለኛ ፡ አክብሮት የተሞላበት ፡አካታች ና ጥንካሬን መሰረት ያደረገ ቋንቋ፤መልእክት ና ምስል በመጠቀም።

ፍርሃት መፍጠር ላይ መሰረት ያደረገ መልእክት ና ምስል በመቃወም እና በማስወገድ።

በስኳር ህመም ምክንያት የሚደርሰውን መድልዎ በማውገዝ እና የስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች እኩል ህክምና እና ድጋፍ እንዲሰጥ ጠበቃ በመሆን።

የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች ሁሉ ፍትሃዊነትን የሚያበረታቱ ተነሳሽነቶችን፣ ፖሊሲዎችን እና ህጎችን ማበረታታት።

ይህንን ቃል ስገባ፣ ከዛሬ ጀምሮ፣ በስኳር ህመም ምክያት ከሚመጣ መገለልና መድልዎ እና መዘዞቹ የፀዳች፣ እንዲሁም ለስኳር ህሙማን የላቀ አክብሮት ና ርህራሄ ያላት ዓለም ለመፍጠር እኔ ቁርጠኛ ነኝ።
Share for greater impact